አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም አመራር እና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚህ ወቅት ÷ በዛሬው ዕለት የተቋሙአመራር እና ሠራተኞች በመላ ሀገሪቱ 250 ሺህ ችግኞችን ይተክላሉ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮጵያ ለምታከናውነው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ዐሻራውን እያሳረፈ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሰባት ዓመታት 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ችግኞችን በ889 ቦታችች መትከሉን ጠቁመው÷ ከተተከሉት ውስጥ 82 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን አስረድተዋል፡፡
በቅድስት አባተ

