Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አረንጓዴ ዐሻራ የቡና ምርት በመጠን እና በጥራት እንዲጨምር አድርጓል – አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የቡና ምርት በመጠን እና በጥራት እንዲጨምር አድርጓል አሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዐሻራቸውን አኑረዋል።

አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት÷ አረንጓዴ ዐሻራ የመደመር መንግሥት እና ህዝብ በአንድ ሀሳብ እና በአንድ ዓላማ ተናበው ርብርብ እያደረጉ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሲካሄድ መቆየቱን አስታወሰው፤ በመርሐ ግብሩ ለኢኮኖሚው እና ለምግብ ዋስትና ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ችግኞች መተከላቸውን ገልፀዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የቡና ምርት በመጠንም በጥራትም እያደገ ይገኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በዚህም ከቡና የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ መጥቷል ነው ያሉት፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version