👉 ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጠዋት ጀምሮ ተስፋን እየተከልኩ ነው ፤ በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ በእስካሁን ሒደት ውስጥ ከ21 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡
👉 በዚህም ከ650 ሚሊየን በላይ ችግኝ ተተክሏል ፤ በቀሩት ሰዓታት ውስጥ ቀሪውን 150 ሚሊየን ችግኝ ከተቻለ ደግሞ ጨምረን እንተክላለን፡፡
👉 ዛሬ ተስፋን የምንተክልበት ቀን ስለሆነ ደስ ብሎኛል ፤ ቦታ እየቀያየርኩ እና ሀገር በቀል የሆኑ ችግኞችን እየመረጥኩ እየተከልሁ ነው፡፡ሌላውም ሰው እንደኔ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
👉 የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት መትከል የምግብ ዋስትናን፣ የገቢ ፈጠራንና የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
👉 አረንጓዴ ዐሻራ ከችግኝ ተከላ ባሻገር ተስፋን፣ አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ ሀብት የመተው ዕሴትን የሚያጠናክር ሀገራዊ ንቅናቄ ነው፡፡
👉 ለሌላ ጉዳይ ምናውለውን ጊዜ ለአረንጓዴ ዐሻራ አውለናል፤ስንተክል ውለናል ፤ የታየው ርብርብ ሕብረታችንን፣ አንድነታችንን ከሁሉ በላይ ደግሞ ለልጆቻችን አንድ ቁም ነገር ትተን ለማለፍ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው፡፡
👉 ኢትዮጵያውያን ለሚፈልጉት ነገርና ለሀገራዊ ክብር በጋራ ይቆማሉ፤ በረባ ባልረባው ኢትዮጵያን መተንኮስ አያዋጣም ፤ ተስማምተን ተግባብተን ብንሰራ ይሻላል፡፡
👉 በጋራ ተስፋን በመትከል የዛሬን የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ግብ ለማሳካት ወደፊት እንቀጥል፡፡
👉 አድካሚ ሊሆን ይችላል፣ ነግር ግን በገባነው ቃል መሰረት መትከል አለብን፣ ቃልን እንደማክበር፣ ቃልን እንደመፈፀም፣የተናገሩትን ነገር ሳያንጠባጥቡ እንደመከወን አኩሪ ተግባር የለም፡፡
👉 በሚያስደምም ተስፋ ላይ ነው ያለነው ፤ኢኮኖሚያችን በጥሩ ሒደት ላይ ይገኛል ፤ እየለማን ነው፤ ከተሞቻችን እየተቀየሩ ነው ያሉት፡፡
👉 ነገር ግን ለዚህ እድገት መሰረት የሚሆን ነገር ካልጣልን ሁሉ ነገር ዋጋ የለውም፤ አፈራችን ተሸርሽሮ እንዳይሄድ ማስቀረት አለብን፣ አካባቢን አረንጓዴ ማድረግ፣ ሀገር በቀል ዛፎችን መትከል፣ ከዚያም ውስጥ ደግሞ ለምግብ የሚሆኑ ችግኞች እንዲወጡ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
👉 ቀደም ሲል በተከናወኑ አረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች በአቮካዶ ምርት ከአፍሪካ 2ኛ ላኪዎች መሆን ችለናል ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች ከተጠናከሩ አንደኛ መሆን እችላለን፡፡
በሚኪያስ አየለ

