አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በእስካሁኑ ሂደት ከ765 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል አሉ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፡፡
ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር እስካሁን 24 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።
እስካሁን ባለው ቆይታም ከ278 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መሸፈኑን በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
የመርሐ ግብሩ አፈጻጸም የመደመር መንግሥት የመፈጸም ዓቅም የታየበት እንደሆነም አንስተዋል።
በመልካም ፈቃዱ

