Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቤንች ሸኮ ዞን የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቤንች ሸኮ ዞን የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን መርቀው ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የመደመር መንግሥት ሰው ተኮር በመሆኑና የዜጎችን ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይሩ ሥራዎች በማከናወን የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ነው፡፡

ለዚህም በተለያዩ አካባቢዎች የገጠሩን ማሕበረሰብ ህይወት ለማሻሻል እየተገነቡ የሚገኙ ሞዴል መንደሮች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

መንደሮቹ የጓሮ አትክልትና የሌማት ትሩፋት ፓኬጆችን ጨምሮ አስፈላጊ መሠረታዊ አቅርቦቶችን እንዳሟሉ አስረድተዋል፡፡

በክልሉ በአሁኑ ወቅት በ16 ወረዳዎች የተገነቡ 16 ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታቸው መጠናቀቁን አመልክተዋል፡፡

በ2019 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች ተመሳሳይ ሞዴል መንደሮችን ለመገንባት እቅድ መያዙን ነው የገለጹት፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ

Exit mobile version