Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱንና ጥንካሬውን በተግባር ያረጋገጠበት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ስኬት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን እና ጥንካሬውን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ሥራ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንዳሉት÷ አረንጓዴ ዐሻራችን እንደ ትውልድ ያሳካነው እና የመተባበርን ውጤት አድምቀን የጻፍንበት ብሔራዊ ድላችን ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ዐሻራችንን አሳርፈናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች በሕብረት ከወጡና ክንዳቸውን ለትብብር ከዘረጉ ሁሌም ድል መኖሩን አውስተው÷ ሁሌም ማሸነፍ፤ ሁሌም መፈጸም መኖሩን ዛሬም ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ጊዜያት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች ታሪክ መሰራቱን ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ ዛሬም እንደ ሕዝብ በምንም ሳንለያይ ባደረግነው ከፍተኛ ርብርብ ውጤት አስመዝግበናል ሲሉ አመልክተዋል።

የዘንደሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እንደ ቀደሞቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን እና ጥንካሬውን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ሥራ እንደነበርም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version