Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አርሰናል ብሩኖ ጉማሬሽን ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ብሩኖ ጉማሬሽን ከኒውካስል ዩናይትድ ለማስፈረም ተስማምቷል።

አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር 75 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍል ይሆናል።

የ28 ዓመቱ ተጫዋች በመድፈኞቹ ቤት ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ውል እንደሚፈራረም ተመላክቷል።

ጉማሬሽ በሚቀጥሉት ቀናት የሕክምና ምርመራውን በማድረግ ዝውውሩን በማጠናቀቅ አርሰናልን የሚቀላቀል ይሆናል።

ከብሩኖ ጉማሬሽ የሽያጭ ትርፍ ላይ የቀድሞ ክለብ ሊዮን ከሰባት እስከ ስምንት ሚልየን ፓውንድ እንደሚያገኝ ዘአትሌቲክ ዘግቧል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version