Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አመካካሪዎቻችን የተሰጣቸውን ሚና በትክክል እየተወጡ ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) አመካካሪዎቻችን የተሰጣቸውን ሚና በትክክል እየተወጡ ነው አሉ፡፡

መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ሂደት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ የስልታዊ ቡድን ላይ ሀሳብን አጥርቶ ለመሄድ ጥረት ተደርጓል።

አንዳንድ ቡድኖች ላይ ሀሳቦች በፍጥነት የሄዱበት ሁኔታ እንዳለ ጠቅሰው፤ የተወሰኑ ቡድኖች ላይ አጥርቶ የመሄድ ጥረት እንዳለ ጠቅሰዋል።

የ500 ቡድን ውይይት ነገ የሚጀመርበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።

የስልታዊ ቡድኑ የምክክር ሂደት ላይ ወደ ምክረ ሀሳብ መግባባት የተደረሰ የሚመስሉ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

አመካካሪዎች የተሰጣቸውን ሚና በትክክል እየተወጡ ነው በማለት ገልጸው፤ አልፎ አልፎ አመካካሪዎችም ሆኑ እኔንም ጨምሮ ለተመካካሪዎች የምንሰጠው ግብዓት ትክክለኛውን አቅጣጫ ማሳየት እንጂ የእኛን አቋም እንዲይዙ ማድረግ በጭራሽ አይፈቀድልንም ሲሉ አረጋግጠዋል።

Exit mobile version