Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው በክልሉ መንግሥት አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ እቅጣጫዎች ላይ ይመክራል።

በተጨማሪም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በኦዲት ቢሮና በምክር ቤት ጽ/ቤት አፈጻጸምና ቀጣይ እቅዶች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፡፡

ምክር ቤቱ በጉባኤው የክልሉ የ2019 አጠቃላይ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

Exit mobile version