አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተወዳዳሪዎች አስደናቂ ብቃት የጀመረው ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 በነገው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል።
የሙዚቃ ባለሙያዎችን፣ የሙዚቃ ወዳጆችን እና መድረክ ያጡ ባለተሰጥኦ ድምፃውያንን በአንድ ያገናኘው ፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምፃውያን ውድድር ያለማቋረጥ ለ7 ዓመታት ተጉዟል።
በነገው የምዕራፍ 23 ውድድር የምድብ አንድ ሰባት ተወዳዳሪዎች ከኮከብ ባንድ ጋር በሁለት ዙር ስራቸውን በማቅረብ ይፎካከራሉ።
የምዕራፉ ውድድር ለ13 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በተመልካቾች የአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይዳኛል።
ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ ይወዳደራሉ።
በምዕራፉ ለፍፃሜ ውድድር ለሚደርሱ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ አራቱም የፍጻሜ ተፋላሚዎች ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
ነገ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የምዕራፍ 23 የሶስተኛ ሳምንት ውድድርን ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በሁለቱ የፋና ቴሌቪዥኖች እና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ፤ አጭር የጽሁፍ መልዕክት በመላክ የውድድሩ ዳኝነት አካል ይሁኑ።

