Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የከተማችንን የስሉጥ ከተማ ግንባታ በተመለከተ ለቤኒን ልዑካን ልምድ አካፍለናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ ኢኖቬሽንና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የልዑካን ቡድኑን ተቀብለን በከተማችን እየተገበርነው ያለውን የስሉጥ ከተማ (Smart City) ግንባታ በተመለከተ ልምድ አካፍለናል ብለዋል።

በተለይም በዋና ዋና ግቦች ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የህዝብ ተሳትፎ፣ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ስራዎችን በተመለከተ ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ አድርገናል ነው ያሉት።

Exit mobile version