አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ የስራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሔድ ጀምሯል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ በጉባኤው ላይ ባቀረቡት የ2018 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዳሉት፥ በክልሉ ከ403 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ለማውጣት ተመዝግበዋል።
በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በክልል ደረጃ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።
በክልሉ በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ከ41 በላይ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መግባታቸውን ገልጸው፥ እስካሁን ድረስ ከ16 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸውን ነው ያነሱት።

