Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ክልል የ2019 በጀት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሆነ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የ2019 በጀት 33 ቢሊየን 253 ሚሊየን 416 ሺህ 348 ብር አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ተመላክቷል፡፡
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ም/ኃላፊ ደረሳ መሐመድ ÷ በጀቱ ከክልሉ መደበኛ ገቢ፣ ከፌደራል መንግሥት ድጎማ፣ ከተጨማሪ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦችና ሌሎች ምንጮች የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በያሲን ኑር
Exit mobile version