Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) የምክክር ጉባዔውን አሁናዊ ሒደት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ተቀናጅተው 500 አባላት ላሏቸው 8 የስራ ቡድኖች መቅረብ ጀምረዋል።

👉 የ250 አባላት ያሏቸው ሁለት ስልታዊ ቡድኖች በአንድ አጀንዳ ላይ የተነጋገሩበትን ሀሳቦች በማጠናቀር እና በመሰነድ ለ500 አባላት ላሏቸው ቡድኖች እያቀረቡ ይገኛሉ።

👉 500 አባላት ያሏቸው ቡድኖች የቀረቡላቸውን ሀሳቦች በማዳመጥ መካተት ያለበትን እና ሊካተት የሚገባውን ሃሳብ በጥልቅ ውይይት እያዳበሩ ነው።

👉 የሥራ ሒደቱን ጨርሰው ለ500 ቡድናቸው ያቀረቡ እንዳሉ ሁሉ፣ ያላጠናቀቁት ደግሞ ስራቸውን አጠናቅቀው ሲጨርሱ ለቀጣዩ ቡድን ያስረክባሉ።

👉 የምክክር ሒደቱ የመጀመሪያ ምዕራፎች በባህሪያቸው ብዙ አለመግባባቶች፣ የስሜት ጫናዎች እና ክርክሮች የሚታዩባቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

👉 አለመግባባቶች የሚፈጠሩት የራስን ምክረ ሀሳብ ወደፊት ለማስቀደም ካለው ፍላጎት እና ለዘመናት ሲጠየቁ የነበሩ የአካባቢ ጥያቄዎችን ለማንጸባረቅ ካለ እምነት የተነሳ ነው።

👉 የሰዎችን ሀሳብ መደፍጠጥ፣ ማሸማቀቅ እና ማሳፈር በስብሰባው የሥነ ምግባር ደንብ ጭራሽ የማይፈቀድ እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

👉 ወሳኝ መርሆች በሆኑት መከባበር፣ መደማመጥ እና ወደ መሀል መምጣት በነጻነት ተነጋግሮ እና ተደማምጦ ወደጋራ ሀሳብ መድረስ ይገባል።

👉 ሀገርን ማዕከል በማድረግ ከየአካባቢው ይዞ የተመጣውን ጥያቄ ብቻ ለመመለስ ሳይሆን ሀገራችን ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጎ መንቀሳቀስ ተገቢ ነው፡፡

👉 በምክክር ሒደቱ እስካሁን ድረስ በአንድም አጀንዳ ላይ የተሰጠ ምንም አይነት ውሳኔ የለም፤ ወደፊትም ቢሆን ውሳኔ አይሰጥም።

👉 የጉባዔው ዋና ተግባር ምክረ ሀሳብ ማዘጋጀት ሲሆን፣ ከጉባዔው መጠናቀቅ በኋላ የተዘጋጁት ምክረ ሀሳቦች ለሕግ አውጪው፣ ለህግ አስፈጻሚው፣ ለሕግ ተርጓሚው እና ለሚመለከታቸው አካላት ይተላለፋሉ።

በዮናሰ ጌትነት

Exit mobile version