አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአንድ ሀገር የሕዝቦች ሰላምና ደህንነት፤ ሕልውና እና ሉዓላዊነት መሰረቱ አስተማማኝ እና ዘመናዊ የመከላከያ ተቋም መኖር ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በታሪኩ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባለፈ የሕዝብ አለኝታነቱን በተግባር ያረጋገጠ የሕዝብ ሠራዊት ነው።
በመደመር መንግሥት እሳቤ አቅጣጫ ጠቋሚነት ሠራዊቱ አጠቃላይ አደረጃጀቱን፣ ዝግጁነቱን እና የውጊያ አቅሙን በማዘመን የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅ ጠንካራ የደህንነት ጋሻ ሆኖ ወጥቷል።
ሠራዊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ ሀገርን እና ሕዝብን ብቻ የሚያገለግል ፕሮፌሽናል ተቋም እንዲሆን እንዲሁም ሙያዊ ብቃቱን ማሳደግ ተችሏል።
የሀገርን የደህንነት ስጋቶች አስቀድሞ ለመከላከል ጊዜውን የዋጁ ዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የመታጠቅ ስራ ተከናውኗል።
የአየር ኃይሉን በዘመናዊ የውጊያ አውሮፕላኖች፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች እና የራዳር ቴክኖሎጂዎች ከማደራጀት ባለፈ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል እንደገና እንዲቋቋም እና እንዲደራጅ ተደርጓል።
የመከላከያ ኢንጅነሪንግ እና የኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን በማጠናከር ሠራዊቱ የሚያስፈልጉትን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች፣ የመጓጓዣ እና የቴክኖሎጂ ግብዓቶች በሀገር ውስጥ የማምረት እና የማደስ አቅሙ ጎልብቷል፡፡
በዘመናዊው ዓለም የሚሰነዘሩ የሳይበር እና የቴክኖሎጂ ስጋቶችን ለመመከት የሚያስችል አቅም በመከላከያ ተቋማት ውስጥ በመገንባት የመከላከል አቅሙ የጸና ነው፡፡
ሀገር ከመጠበቅ ባሻገር በሀገራዊ የልማት እንዲሁም በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ወቅት ለሕዝብ ፈጣን እርዳታ በመስጠት ሕዝባዊነት መሰረት መሆኑን እያስመሰከረ ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች በመመከት የሉዓላዊነት ዋስትና መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል።
በተለይም ሀገርን ለማፍረስ እና ለማዳከም የተቃጡ የተለያዩ የውስጥ እና የውጭ የደህንነት ስጋቶችን በመመከት፣ የሕዝቦችን አብሮነት እና የሀገርን አንድነት አስከብሮ ለማስቀጠል የከፈለውን ዋጋ ሕዝቡ በከፍተኛ አክብሮት ይመለከተዋል።
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎረቤት ሀገራት እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚካሄዱ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት የኢትዮጵያን መልካም ስም ያገነነ እና የቀጣናውን ሰላም ያስከበረ የሰላም ዘብም ነው።
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በመደመር እይታ በተካሄዱ አጠቃላይ ተቋማዊ እና የቴክኖሎጂ ሪፎርሞች ከቀደመው ጊዜ በላይ ጠንካራ፣ ዘመናዊ እና ዝግጁ የሆነ ተቋም ለመሆን በቅቷል።
ዘመኑን የዋጁ ጦር መሳሪያዎችን የታጠቀው ሠራዊቱ ሊቃጣ የሚችልን ትንኮሳ በሩቁ ከማስቀረት ባለፈ ውጊያን በትንሽ ኪሳራ በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡
መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የሕዝቦችን ሰላም እና ሕልውና የሚያስክብር አስተማማኝ የኢትዮጵያ ደህንነት ጋሻ ሆኖ ቀጥሏል።
በመልካም ፈቃዱ

