Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገራዊ ምክክሩ ሁለት ተጨማሪ ቡድኖች በተመካከሩባቸው ምክረ ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርዓት እንዲሁም በሙስና እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ ዘዴ መሰረት እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው ስምንት ቡድኖች የተዋቀሩ ሲሆን፥ እያንዳንዱ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ምክክር እያካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህም በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርዓት እንዲሁም በሙስና እና መልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ የቆዩ ሁለት ቡድኖች በተጠናቀሩ ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በቃለ ጉባዔ ላይ ፈርመዋል፡፡

በተመሳሳይ ቀደም ሲል በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ የቆዩት ሌሎች ሁለት ቡድኖች በምክረ ሃሳቦቻቸው ላይ ተስማምተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባዔ ላይ መፈራረማቸውን ኮሚሽኑ መግለጹ ይታወቃል፡፡

የሌሎች አጀንዳዎች ተመካካሪዎችም በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን የጋራ አድርገው በቃለ ጉባዔዎቻቸው ላይ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version