Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፒኤስጂ ከአስቶንቪላ – ተጠባቂው ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በፒኤስጂ እና አስቶንቪላ መካከል ይደረጋል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ እና የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አስቶንቪላ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ፒኤስጂ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ለማንሳት የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
አስቶንቪላ በፈረንጆቹ 1982 ያሳካውን የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ ከበርካታ ዓመታት ጥበቃ በኋላ ዋንጫውን ለማንሳት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦስትሪያ ሬድ ቡል አሬና የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
Exit mobile version