Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ይበልጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው – አቶ አወሉ አብዲ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ፡፡
17 የመንግሥት ጽሕፈት ቤት አገልግሎቶችን በውስጡ የያዘው የጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሕንጻ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
አቶ አወሉ አብዲ በዚህ ወቅት ÷ ሕንጻው ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ ዲጂታል አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማዘመን እስከ ቀበሌ ያሉ መዋቅሮች በዘመናዊ መልኩ እየተደራጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በወርቃፈራሁ ያለው
Exit mobile version