Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጂንካ ዲስትሪክት የዲመካ መለስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ዲስትሪክት የዲመካ መለስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀምሯል፡፡
በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ግንባታውን አስጀምረዋል፡፡
ግንባታውን የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር በመተባበር እንደሚያከናውኑት ተገልጿል፡፡
የዲመካ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጠናቅቆ ሥራ ሲጀምር ለኢንቨስትመንት መስፋፋትና ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የክልሉ የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢዲሬ እርኮ (ኢ/ር) በበኩላቸው ÷ ግንባታው በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
Exit mobile version