Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምክክር ጉባዔው በየቡድኖች የተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦችን የማጣጣም ሥራ እየተጠናቀቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው በየቡድኖቹ የተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦችን የማጣጣም ሥራ እየተጠናቀቀ ነው አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ፡፡
የሀገራዊ ምክክር ም/ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ሥላሴ የሀገራዊ ምክክሩን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም የጉባዔው ተሳታፊዎች እያንዳንዱ ቡድን 15 ተወካዮችን መርጦ በየቡድኑ ተጠናቅረው የሚገኙ ምክረ ሃሳቦችን ለማጣጣም ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
የእነዚህ ተወካዮች ዋና ሥራ በየ ቡድኑ ብዙ ጊዜ ተፈጅቶባቸው የተዘጋጁ ምክረ ሃሳቦችን ማጣጣም መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በዚህም በ8 ቡድኖች ምክረ ሃሳቦች መካከል ተቃርኖና ድግግሞሽ ሳይፈጠር ወጥ በሆነ መልኩ እንዲቀርብ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም የተመረጡት ተወካዮች ስለ ሌሎች ቡድኖች ምክረ ሃሳቦች ግንዛቤ የወሰዱ ሲሆን ÷ በዚህም እርስ በርስ በመነጋገር ሃሳቦችን ያጣጥማሉ ነው ያሉት፡፡
በአሁኑ ወቅትም በምክክር ጉባዔው በየቡድኖች የተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦችን የማጣጣሙ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡
Exit mobile version