አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 212 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ተመላሾቹ 2 ሺህ 210 ወንዶች፣ 1 ሴት እና 1 ጨቅላ ሕጻን ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ መካከልም 38 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኛሉ።
መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ94 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ በትብብር እየተከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

