Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአራዳ ፓርክ ለሥራ እድልና ለቱሪዝም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የተገነባው የአራዳ ፓርክ ለሥራ እድልና ለቱሪዝም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው አሉ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ፓርኩ ለሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የቀረበ የከተማችን ስጦታ ነው ብለዋል፡፡
ፓርኩ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች አካታች በሆነ መንገድ በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ቱሪዝምን በማሳደግ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፥ ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በውቡ አራዳ ፓርክ በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ በማለት ጋብዘዋል፡፡
Exit mobile version