Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዓባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ የግብጽን የማደናገር ዘመቻ መመከት ይገባል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ለዘመናት የቆ የተዛባ ትርክትን የቀየረ ነው አሉ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)።
አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)÷ በኢትዮጵያውያን ጽኑ ትብብር የተገነባው የሕዳሴ ግድብ የዓባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ለዘመናት የቆየ የተዛባ አረዳድን የቀየረ መሆኑን ተናግረዋል።
ግድቡ የትኛውንም ሀገር እንደማይጎዳና ይልቁንም ቀጣናውን በኢነርጂ እያስተሳሰረ መሆኑ በተግባር መረጋገጡን አስገንዝበዋል፡፡
ነገር ግን ግብጽ ይህንን እውነታ በመካድ አሁን ላይ የቀደመ በጩኸት የማደናገር ተግባሯን በስፋት እያከናወነች መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ዓባይ የተፋሰሱ ሀገራት በትብብር የሚጠቀሙት ሃብት እንጂ የግብጽ የግል ንብረት አይደለም ያሉት አረጋዊ (ዶ/ር)÷ ከዚህ አኳያ የግብጽ የማደናገር ዘመቻ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ዋነኛ ዓላማ በትብብር ማደግ መሆኑን አውስተው÷ ግብጽ ከዓባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የምታሰራጫቸውን መሰረተ ቢስ ውንጀላ መመከት እንደሚገባ አጽንኦትሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በትብብር ምን ማሳካት እንደሚችሉ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማሳየታቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይ በርካታ ግድብ የመገንባት አቅሙም ዝግጁነቱም አላቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት ሕዝብን በማስተባበር ረገድ በርካታ ጠቃሚ ልምድ መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
ይህን የሕዳሴ ግድብ ልምድ በቀጣይ ለሚከናወኑ መሰል የልማት ሥራዎች ትልቅ ግብዓት መሆኑንም አብራርተዋል።
Exit mobile version