Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፌዴራል ፖሊስ የፀጥታ ስጋቶችን በላቀ ብቃት ለመመከት ዝግጁ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ስጋቶችን በላቀ ብቃት በማክሸፍ የሀገርን ሰላም ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው አሉ የፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ስትራቴጂክ አመራሮችና ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፀጥታ እቅድ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት ÷ ተቋማቸው የሠራዊቱን ሥነ ልቦና በመገንባት፣ የወትሮ ዝግጁነት በማጠናከርና የማድረግ አቅሙን ይበልጥ በማሳደግ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እድገት እያሳየች ባለችበት ወቅት ሰላሟንና እድገቷን የማይፈልጉ አካላት የደቀኑትን የፀጥታ ስጋት ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍለን ለማክሸፍ ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ በሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ እና በወትሮ ዝግጁነት ላይ ያተኮረ የመወያያ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version