Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ያለማቋረጥ ለሰባት ዓመታት እየተካሄደ የሚገኘው ፋና ላምሮት በመጪው ቅዳሜ በምዕራፍ 23 ከምድብ አንድ 6 ተወዳዳሪዎች ጋር ቀጥሎ ይካሄዳል።

በቅዳሜው የምዕራፍ 23 ውድድር የምድብ አንድ ተወዳዳሪዎች ከኮከብ ባንድ ጋር በሁለት ዙር ስራቸውን ያቀርባሉ።

ለ13 ሳምንታት የሚቆየው የቅዳሜ የ5ኛ ሳምንት ውድድር በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በተመልካቾች የአጭር ጽሑፍ መልዕክት ይዳኛል።

በምዕራፉ ፍፃሜ የሚቀሩ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን የሚካሄደውን ውድድር 6 ሰዓት ላይ በሁለቱም የፋና ቴሌቭዥንና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።

በለምለም ዮሐንስ

Exit mobile version