Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመውሊድ በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና አብሮነትን በማጠናከር ሊሆን ይገባል – ጠቅላይ ምክር ቤቱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ልደት በዓልን ስናከብር በነብዩ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይገባል አለ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የ1 ሺህ 501ኛውን የታላቁ የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓልን (መውሊድ) አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ነብዩ በሕይወት በነበሩ ጊዜ ለሁሉም አዛኝ እንደነበሩት ሁሉ የሰው ልጅም እንዲሁ አዛኝ መሆን እንዳለበት በመግለጫው ተወስቷል፡፡
የነብዩን አስተምህሮ በማስታወስ የተቸገሩትን በመርዳት ዕለቱን ማሳለፍ እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡
በዓሉ “የፍትሁ ነብይ” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ማክሰኞ በአንዋር መስጅድ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር የመውሊድ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
ኮሚቴው ለነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በፈቲያ አብደላ
Exit mobile version