አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳ ከአስቶን ቪላ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
የ28 ዓመቱ ተጫዋች ለመድፈኞቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ በሰጠው አስተያየት፥ እዚህ የተገኘሁት ለአሸናፊነት ነው፤ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ ሲል ተደምጧል፡፡
በዓለማችን ካሉ ምርጥ ክለቦች አንዱ የሆነውን አርሰናል መቀላቀል ለእኔ ትልቅ ክብር ነው ያለው ተጫዋቹ፤ የክለቡን ስኬት ለማስቀጠል ያለኝን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ሲል ተደምጧል፡፡
ኮንሳ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለአራት ዓመታት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን፤ 15 ቁጥር ማሊያ እንደሚለብስ ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡

