Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመሳሪያ መነጋገር ከአሁን በኋላ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀራል – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአሁን በኋላ በመሳሪያ መነጋገር በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀራል አሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፡፡
ከመላው ሀገሪቱ በሕዝቡ በተወከሉ 4ሺህ ተመካካሪዎች መካከል ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የጉባኤው አባላት ባለፉት 46 ቀናት ኢትዮጵያን አጀንዳቸው በማድረግ ላደረጉት ተሳትፎና ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ባለፉት የምክክር ጊዚያት ያሳዩት መፋቀርና መከባበር የኢትዮጵያውያን ልዩ መገለጫ መሆኑን ለዓለም አሳይተዋል ብለዋል፡፡
ምክክሩ ኢትዮጵያውያን ከተመካከሩና ከተወያዩ ውጤት እንደሚያመጡ አስተምሮ ያለፈ ነውም ብለዋል፡፡
ይህ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካና ለዓለም የሚበቃ ተሞክሮ መስጠቱን በመጥቀስ፤ በመሳሪያ መነጋገር ከአሁን በኋላ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀራል ነው ያሉት፡፡
በአቤል ነዋይ
Exit mobile version