Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው፡፡
👉 በሀገራችን የነበሩትን ታሪካዊ ስብራቶች እንዲሁም የሐሳብ ልዩነቶች በጠብመንጃ እና በኃይል ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ በምክክር ለመፍታት የሚያስችል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል፡፡
👉 ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ተካሂዷል፡፡
👉 ማንኛውም የህብረተስብ ክፍል ሳይገለል፤ የሁሉም ድምጽ እንዲሰማና እዲከበር በትኩረት ተሰርቷል፡፡
👉 በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ከአራቱም የሀገራችን ማዕዘናት 4 ሺህ ተመካካሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
👉 በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችሉ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ምክከሮች ተካሂደዋል፡፡
👉 አጀንዳዎቹ የሀገራችንን መሰረታዊ ችግሮች የዳሰሱና ለነገዋ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጥሉ ናቸው፡፡
👉 በመደማመጥና በመከባበር ለሀገራችን የተሻለ መፍትሄ በጋራ መፈለግ መቻላችን፤ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ፈተና አውጥተው ወደተሻለ እና አዲስ ምዕራፍ የሚሻግሩ ናቸው፡፡
👉 ይህ የጀመርነው የመደማማጥ ባህል ደምቆ ለትውልድ እንዲሻገር፤ ዘላቂ እሴታችን ይሆን ዘንድ የሁላችንም ቁርጠኝነት ያሰፈልጋል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው

Exit mobile version