Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ምክክሩ ፖለቲካዊ ተቃርኖ በይቅርታና በምክክር ጎዳና እንዲተካ መሰረት ጥሏል፡፡
👉 ውጤቱ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ነው፡፡
👉 የሀገር ብርታት ያለው ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በውይይት መፍታት ላይ ነው፡፡
👉 የዛሬዋ እለት ድምቀቷ እና ቁም ነገሯ ለሀገር የሚበጅ ለትውልድ የሚዋጅ አንድነታችንን የሚያጸና መልካም ተስፋችንን የሚያለመልም ሁኔታን የሰማንባት መሆንዋ ነው፡፡
👉 የ130 ሚሊየን ህዝብን ሀሳብ ተሸክሞ ኃላፊነት ውሰድ ቀላል አይደለም፡፡
👉 ተመካካሪዎች የነገን የህብር አንድነት እንድናይ፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረጋችሁ ታሪካዊ ስኬት ነው፡፡
👉 በምክክሩ ለነገው ትውልድ የሚሻገር አሻራ ተቀምጧል፡፡
👉 በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ሃሳቦች ለፖለቲካዊ ልምምዳችን እና ለሀገር ግንባታ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡
👉 ምክክሩ የሁላችንም የሆነችውን ኢትዮጵያ የሚገልጹና የሚያጹኑ የጋራ ርዕይ እና እጣ ፈንታ በአንድ ላይ ለማስኬድ የሚያስችል እውቀት የተጨበጠበት ነው፡፡
👉 የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳ በመከባበር እና በሰመረ ቋንቋ ከኃለ ቃል በጸዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን አሳይቷል፡፡
👉 በማህበራዊ አውዳችን ውስጥ መልክ መያዝ የሚኖርባቸዉ የፖለቲካ ቃላት እና ስንኞች ሰከን ያሉ እንዲሆኑ ተጨባጭ ልምድ ሰጥቷል፡፡
በእመቤት ሲሳይ

Exit mobile version