አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡
አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ነው የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዳግም ማሻሻል የቻለው፡፡
ዮሚፍ ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በሊዝበን ያስመዘገበውን የ57 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ የቀድሞ ክብረ ወሰን በ29 ሰከንዶች አሻሽሏል።

