አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚከበረውን 1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) ምክንያት በማድረግ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ ይተኮሳል አለ መከላከያ ሚኒስቴር፡፡
መድፉ ነገ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ እንደሚተኮስ በሚኒስቴሩ የመከላከያ ስፖርትና ኪነ ጥበባት ሥራዎች ማዕከል ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ስለሆነም የመዲናዋ ነዋሪዎች በጉዳዩ ላይ ተገቢው መረጃ እንዲኖራቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስገንዝቧል፡፡

