Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ…ጃላል ግርማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ ኩሳ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591 ነጥብ 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 አጠቃላይ ውጤት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው በአዳማ የሚገኘው የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ተማሪ ጃላል ግርማ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ 591 ነጥብ 6 ውጤት በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የኦሮሚያ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ደጀኔ ኢቲቻ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡

Exit mobile version