Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደባርቅ ከተማን የቱሪስት መዳረሻነት ለማጠናከር ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያ በር የሆነችውን ደባርቅ ከተማ ለማዘመንና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በዚህ ወቅት ÷ ኢትዮጵያ በጉያዋ ከያዘቻቸው የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መሆኑን አንስተዋል።

ይህን ድንቅ ሥፍራ ለመጎብኘት ከተለያዩ ዓለማት የሚመጡ ዜጎች ማረፊያ የሆነችው ደባርቅ ከተማ ለዚህ የሚመጥን መሠረተ ልማት ሳትገነባ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት በመግለጥ ለጎብኝዎች ምቹ አድርጎ ለመጠቀም ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡

ከተማዋን የማልማትና ለጎብኝዎች ምቹ የማድረግ ሥራ ለአንድ ወገን የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአንዷለም ተስፋዬ

Exit mobile version