Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሁሉም አማራጮች የአህጉሪቱን የጤና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ይገባል – መሐሙድ አሊ ዩሱፍ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የአህጉሪቱን የጤና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ተግባር ሊሆን ይገባል አሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፡፡
በአምስት የጤና ዘርፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ለአራት ቀናት የሚቆየው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ አባል ሀገራት የዜጎቻቸውን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ዘላቂነት የሚያረጋግጡ አቅሞችን መገንባት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የአፍሪካን ጤና ሥርዓት ዘላቂነት በአስተማማኝ መሠረት ለመገንባት የፋይናንስ አቅምን በማጎልበት የምርምርና ፈጠራ አቅሞችን ማሳደግ እንደሚገባም አመልክተዋል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጭብጥ አፍሪካውያንን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሻሻል በውሃና ንፅህና አጠባበቅ ላይ ትኩረት አድርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የአህጉሪቱን የጤና ሥርዓት ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
Exit mobile version