Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ እና ታይላንድ የሁለትዮሽ ትብብርን የሚያጠናክር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና ታይላንድ የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ የሚያጠናክር ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የዛሬው ትብብር ለሁለቱ ሀገራት አጋርነት ወሳኝ ነው።

የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ጉብኝትም በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ተብሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው÷ የተፈረመው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት አጋርነት እና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

በተለይም ሁለቱ ሀገራት የደቡብ ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር በተመሳሳይ መንገድ ላይ መሆናቸውን በማንሳትም ይህንን የጋራ ትብብር ለማሳደግ ኢትዮጵያ እና ታይላንድ በጋራ የሚሰሩ ሀገራት ናቸው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው  “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ”ን በይፋ አስጀምረዋል።

በይስማው አደራው

Exit mobile version