Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኤር ፖሊስ የሰራዊቱን የወትሮ ዝግጁነት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ኤር ፖሊስ የሰራዊቱን የወትሮ ዝግጁነት ይበልጥ ሊያጠናክር ይገባል አሉ፡፡

ዋና አዛዡ የኤር ፖሊስ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘት የሥራ ስምሪት ሰጥተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ኤር ፖሊስ ክፍለ ጦር የሀገር መመኪያ የሆነውን የአየር ሃይል ደህንነት በአስተማማኝ በመጠበቅ እና የአካባቢውን ሰላም በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አንስተዋል፡፡

በየደረጃ ያሉ የኤር ፖሊስ አመራሮች ወቅታዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሰራዊቱን የወትሮ ዝግጁነት በማጠናከር በተቋም ደህንነት ጥበቃ እና ደንብ በማስከበር ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረው ሊያሰቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኤር ፖሊስ ክፍለጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ኦርዶፋ ድንቁ በበኩላቸው ÷የክፍለ ጦሩን ወትሮ ዝግጁነት ለማረጋገጥ በየጊዜው የሚካሄድ የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ አቅም መሆኑን ገልፀዋል።

ለኤር ፖሊስ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና በዋናነት በወታደራዊ የአመራር ጥበብ፣ በሰራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ አቅጣጫዎችና በሕግ ግንዛቤ ዙሪያ አመራሩ የተሻለ የመሪነት አቅም እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ መሆኑን የመከላከያ አንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

Exit mobile version