አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለሚያስገነባው የወርቅ ፋብሪካ የማምረቻ መሳሪያዎች አቅርቦት ስምምነት ተፈራርሟል።
ኩባንያው ስምምነቱን የተፈራረመው መቀመጫውን በኦስትሪያ ካደረገው ሴሜንት ኤንድ ማይኒንግ ቴክኖሎጂ (ሴምቴክ) ከተሰኘ የፋብሪካ መሳሪያዎች አምራች ኩባንያ ጋር ነው፡፡
በስምምነቱ መሰረት ሴምቴክ ኩባንያ በዓመት 1 ነጥብ 25 ሚሊየን ቶን ወርቅ አዘል ድንጋይ ፕሮሰስ ማድረግ የሚችል የወርቅ ፋብሪካ ማሽነሪ የማምረትና የመገንባት ተግባር እንደሚያከናውን ተገልጿል።
በተጨማሪም ለፋብሪካው የሚያስፈልጉ ምርቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ በማጠናቀቅ ለሚድሮክ መተከል ወርቅ ፋብሪካ የሚያስረክብ ይሆናል።
ሚድሮክ ወርቅ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር በወርቅ ምርት ላይ የተሰማራ ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በሔኖክ ለሜ

