Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መሬትን ከብክነት ለመከላከል በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋት ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመሬት ሃብትን በአግባቡ በማስተዳደር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን በትኩረት መስራት ይገባል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ያተኮረ ጉባዔ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጉልበት፣ መሬት እና ካፒታል ለኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ ጉዳዮች በመሆናቸው በአግባቡ ማስተዳደርና መጠቀም ይገባል፡፡

መሬትን ከብክነትና ከሕገ ወጥ ወረራ ለመከላከል የመሬት አያያዝ፣ አጠቃቀምና አስተዳደርን ይበልጥ በማጠናከር የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለዚህም የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ ራሱን ችሎ እንዲደራጅ መደረጉን ጠቁመው ÷ ሥራውን ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት ክልላዊና ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞን በተጨባጭ ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በአበበች ኬሻሞ

Exit mobile version