አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ባርሴሎና ለተጨዋቹ ዝውውር 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ አድርጓል፡፡
ጋብሬል ጄሱስ በስፔኑ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2029 ድረስ የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡
የ29 ዓመቱ ተጫዋች ለአርሰናል 123 ጨዋታዎችን አድርጎ 32 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ጋብሬል ጄሱስ አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ የስብስቡ አካል ነበር፡፡
ተጫዋቹ ከአርሰናል በተጨማሪ ለማንቼስተር ሲቲ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የኤፍ ኤ ካፕ፣ የካራባኦ እና የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫዎችን ማሳካቱ አይዘነጋም፡፡

