አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።
በዚህ ሳምንት በእምነት የሸዋስ፣ ሀይለየሱስ ታደገ፣ ፍቅርተ ወርቁ፣ በረከት መስፍን እና ያሬድ ወንድምነህ በኮከብ ባንድ በመታጀብ ስምንቱን ለመቀላቀል ይፎካከራሉ።
በምዕራፉ ፍፃሜ የሚቀሩ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን ውድድር 6 ሰዓት ላይ በሁለቱም የፋና ቴሌቭዥኖችና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።

