Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብራዚል የንግድና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብራዚል የንግድና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ (አፔክስ ብራዚል) ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብራዚል ጉብኝታቸው ወቅት ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር ያደረጉትን ውይይት መነሻ በማድረግ ቢሮው መከፈቱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር መለስ ዓለም ገልጸዋል።
ተቋሙ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብርን በማላቅ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።
ሀገራቱ የብሪክስ አባል እንደመሆናቸው ትብብራቸውን ወደ ተጨባጭ የንግድ ዕድሎች ለመቀየር እገዛ እንደሚያደርግም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም የብራዚል ባለሀብቶች በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ገበያ ያሉ የንግድ እድሎችን ለመመልከት የሚያስችል ነው፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባለሀብቶች በብራዚል ያለውን ዕድል ለመመልከት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በፍቅርተ ከበደ
Exit mobile version