አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያመሩ ነው፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ወጣቶች ወደ ሦስት የአፍሪካ ሀገራት ይጓዛሉ፡፡
24ቱ ወጣቶች ከነገ ጀምሮ ወደ ጋና፣ ዚምባቡዌ እና ናይጄሪያ እንደሚያቀኑ ተናግረዋል፡፡
የልምድ ማካፈል መርሐ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ ቡድን በፓኪስታን በመገኘት የችግኝ ተከላ ማድረጉን አስታውሰዋል።
የወጣቶቹ ጉዞ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ ከማካፈል ባለፈ ትብብርና ወንድማማችነትን ያጠናክራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

