Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” በመባል ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጣቸው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ ‘Act For Early Years’ ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” በመባል እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ”የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት” የተሰጠ ነው።
ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።
እውቅናው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትርና የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ዩኒሴፍ እና ዩኒስኮን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።
እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።
Exit mobile version