Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጋብሬል ማርቲኔሊ አል ሂላልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ማርቲኔሊን ከአርሰናል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

አል ሂላል ለጋብሬል ማርቲኔሊ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ለአርሰናል መክፈሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጋብሬል ማርቲኔሊ በ2025/26 የውድድር ዓመት ከአርሰናል ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።

የማርቲኔሊ የዝውውር ሂሳብ የአርሰናል የተጫዋች ሽያጭ ክብረ ወሰን በመሆን ተመዝግቧል።

አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን በፈረንጆቹ 2017 ሊቨርፑልን  በ35 ሚሊየን ፓውንድ በመቀላቀል የክለቡ የተጫዋት ሽያጭ ክብረ ወሰን ይዞ መቆየቱ ይታወሳል።

Exit mobile version