አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ፍራንክ ጋርሺያ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ግንኙነት ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያና አሜሪካ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ቀደም ሲል የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ልዑካን በዋሽንግተን ዲሲ በመገናኘት በኢኮኖሚ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያና ደህንነት ትብብር እንዲሁም በቀጣናዊ ሰላም እና ደህነት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ውይይት ማድረጋቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

