Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምክር ቤቱ ሥራዎች ውጤታማ የሆኑት በመላው ሠራተኛ አብሮነትና ጥረት ነው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራዎች ስኬታማና ውጤታማ የሆኑት በመላው ሠራተኛ አብሮነትና ጥረት ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ።

በ2018 ዓ.ም በሥራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የዕውቅናና የምስጋና ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባለፉት አምስት ዓመታት በምክር ቤት ለተከናወኑ ውጤታማና አበረታች ተግባራት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

‎ሠራተኞቹ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውን ገልጸው ላሳዩት የላቀ የሥራ አፈጻጸምም ምስጋናቸውን በማቅረብ ሽልማት አበርክተዋል።

በቀጣይ የሚመጡ አዳዲስ የምክር ቤት አባላትን በተለመደው የምክር ቤቱ ደንብና አሠራር መሠረት ተቀብለው በብቃት ሊያገለግሉ ይገባል ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version