Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ በዛሬው ዕለት ሥራ ጀምሯል፡፡
ማዕከሉን መርቀው ሥራ ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሕንጻ የከተማዋን ቀደምት የኪነ ሕንጻ ጥበብ በጠበቀ መንገድ በጥራት ተገንብቶ ተጠናቅቋል፡፡
ማዕከሉ ከሚሰጠው ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት በተጨማሪ ከኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር ተዳምሮ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ሆኗል ነው ያሉት።
Exit mobile version