Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቶኪ በዓ ባህላዊ እሴቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማፋጠን ይገባል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቶኪ በዓ ባህላዊ እሴቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማፋጠን ይገባል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የዳውሮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቶኪ-በዓ” በታርጫ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ተከብሯል።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ቶኪ-በአ ከጥንት ዘመን ጀምሮ አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት በደስታና በፍሥሐ የሚቀበሉበት፣ በተለይ የክረምቱ ዝናብና ዳመና ተገፎ የብርሃን ጸዳል የሚፈነጥቅበት ወቅት ነው፡፡
በዓሉ የሚከበርበት የቀን መቁጠሪያ የጨረቃ ዑደትን ተከተሎ ቀናትና ወራትን በማስላት የተቀመረ እንደሆነ አንስተዋል።
ቶኪ በዓ በተለያዩ ምክንያቶች ተራርቀው የነበሩና የተነፋፈቁት የሚገናኙበት፣ ዘመዳዝማድና ወዳጅ የሚጠያየቁበት፣ የተጣሉት የሚታረቁበት የአንድነት በዓል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በበዓሉ የሚደረገው መሰብሰብ አንድነትና አብሮነትን በማጠናከር ለሕብረ ብሔራዊነት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡
ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን የቶኪ በዓ በዓልን ባህላዊ ዕሴት ጠብቆ ማቆየትና ለወጣቱ ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version