አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ኮቨንትሪ ሲቲን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የማንቼስተር ሲቲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ማንቼስተር ሲቲ ተከታታይ ሦስተኛ ድሉን አሳክቷል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ፉልሃምን 3 ለ 2 ሲያሸንፍ፣ ሊድስ ከብራይተን እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር ከኖቲንግሃም ፎረስት ያለምንም ግብ አቻ ሲለያይ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ከቦርንማውዝ 2 አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ሃል ሲቲ ከ አስቶንቪላ የሚገናኙ ይሆናል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ኮቨንትሪ ሲቲን አሸነፈ

